ጨዋታዎች በPlay ጨዋታዎች መተግበሪያው አማካኝነት ይበልጥ አዝናኝ ናቸው። ያንን ሊተዉት የማይችሉት ጨዋታ ያግኙት፣ ከዚያ ከጓደኛዎችዎ ጋር ይፎካከሩና ስኬቶችዎን ይከታተሉ። በተጨማሪ ጨዋታዎች እየተካኑ ሲመጡ ችሎታዎችዎን በተጫዋች መገለጫዎ ውስጥ ያሳዩ። በተጨማሪም፣ በማንኛውም መሣሪያ ላይ ካቆሙበት መቀጠል ይችላሉ። ሁሉም አንድ ቦታ ላይ፣ በማናቸውም የዓለም ቦታ ላይ ዓለምን ይጫወቱ።
ቁልፍ ባህሪያት
• የተጫዋች መገለጫ፦ የራስዎን ብጁ የተጫዋች መታወቂያ ይፍጠሩ፣ XP ያግኙ፣ እና እርስዎ በመላው Google Play ላይ በጨዋታዎች እየተካኑ ሲመጡ ደረጃዎን ያሳድጉ።
• ስኬቶች እና የመሪዎች ሰሌዳዎች፦ ፈተናዎችን ያጠናቅቁ፣ ሽልማቶችን ያግኙ፣ እና ከመተግበሪያው ሆነው ሁሉንም ይከታተሉ። ከዚያ ከሌሎች ተጫዋቾች ጋር ሲነጻጸሩ እንዴት እንደሆኑ ይመልከቱ።
• አብሮገነብ የGoogle ጨዋታዎች፦ PAC-MAN፣ Solitaire፣ Snake፣ እና ክሪኬት ይጫወቱ — ከመስመር ውጭ ያሉ እንኳ ቢሆኑ።
• የመጫወቻ ማዕከል፦ በአዲስ፣ በመታየት ላይ ያሉ እና የአርታዒያን ምርጫ ስብስቦቻችን ውስጥ አዝናኝ የሆነ ነገር ያግኙ።
• የአጨዋወት ቀረጻ*፦ ከሚወዷቸው የሞባይል ጨዋታዎች ሆነው ምርጥ የአጨዋወት አፍታዎችዎን ይቅረጹ እና ያጋሩ።
* በተወሰኑ አገሮች ውስጥ ብቻ የሚገኝ