Google መልዕክቶች መልዕክት ለመላላክ ይፋዊ የGoogle መተግበሪያ ነው። Google መልዕክቶች አንድ ቢሊዮን የሚሆኑ ተጠቃሚዎች የሚገናኙበት መንገድ ላይ ከፍተኛ ከውጥ እያደረገ ነው እና ኤስኤምኤስ እና ኤምኤምኤስን የሚተካ የጽሑፍ መልዕክት ለመላክ የኢንዱስትሪ ደረጃ በሆነው የበለጸጉ የተግባቦት አገልግሎቶች (አርሲኤስ) የተጎላበተ ነው። በአርሲኤስ ከፍተኛ ጥራት ያላቸው ፎቶዎች እና ቪድዮዎችን ማጋራት፣ በተለዋዋጭ የቡድን ውይይቶች መደሰት እና የiPhone ጓደኞችዎን ጨምሮ ከሌሎች አርሲኤስ ተጠቃሚዎች ጋር እንከን የለሽ በሆነ መንገድ መገናኘት ይችላሉ።
• የበለጸገ ተግባቦት፦ ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን ፎቶዎች እና ቪድዮዎች ያጋሩ፣ ጓደኞች በሚተይቡበት ጊዜ ይመልከቱ እና አሁን ያለ እንከን የiPhone ጓደኞችዎን በሚያካትቱ ተለዋዋጭ የቡድን ውይይቶች ይደሰቱ።
• የግል ስሜት፦ እንደ ብጁ የውይይት አረፋ ቀለማት ወይም አስደሳች GIF የራስ ፎቶዎች ባሉ ባህሪያት ውይይቶችን በልዩ ሁኔታ የራስዎ ያድርጉ።
• የግላዊነት ጉዳዮች፦ የግል ውይይቶችዎ በGoogle መልዕክቶች ተጠቃሚዎች መካከል በመጨረሻ እስከ መጨረሻ ምሥጠራ ጥበቃ እንደሚደረግላቸው ስለዚህም መልዕክት እየላኩላቸው ካሉት ሰው በስተቀር የእርስዎን መልዕክቶች እና ዓባሪዎች ማንም (Google እና ሦስተኛ ወገኖችን ጨምሮ) ማንበብ ወይም ማየት እንደማይችሉ እያወቁ እረፍት ይሰማዎት። በተጨማሪም በላቀ የአይፈለጌ መልዕክት ጥበቃ ይደሰቱ።
• በሰው ሠራሽ አስተውሎት የተጎላበተ መልዕክት መላላክ፦ በአስማት አዘጋጅ ጥቆማዎች እና በቅርብ ጊዜ ሰው ሠራሽ አስተውሎት ባህሪዎቻችን ምርጡን መልዕክት ይንደፉ።
• በመላው መሣሪያዎች ላይ እንከን የለሽ፦ በስልክዎ ላይ ውይይት ይጀምሩ እና ያለ እንከን በእርስዎ ጡባዊ ወይም ኮምፒውተር ላይ ይቀጥሉት። እንዲሁምመተግበሪያው Wear OS ላይ ይገኛል።
Google መልዕክቶች ከመልዕክት መላላክ ብቻ በላይ ነው፤ የበለጠ የበለጸገ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ለመገናኘት የበለጠ ገላጭ መንገድ ነው።
እንዲሁም መተግበሪያ Wear OS ላይ ይገኛል። የአርሲኤስ ተገኝነት በክልል እና አገልግሎት አቅራቢ ይለያያል እና የውሂብ ዕቅድ ሊያስፈልግ ይችላል። የባህሪያት ተገኚነት በገበያ እና መሣሪያ ይለያያል እና የቅድመ-ይሁንታ ሙከራ ምዝገባ ሊያስፈልግ ይችላል።